የክልል ምክር ቤቱ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶችን የኦዲት ግኝቶችን በመገምገም ላይ ይገኛል።
የክልል ምክር ቤቱ የበጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ የ2012-2015 የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝቶችን እየተመለከተ ሲሆን በዚሁ መሰረትም በዛሬው ዕለት ቋሚ ኮሚቴው የክልሉን ፕላን ኮሚሽን፣ የህብረት ስራ ኤጀንሲ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ፣ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንን የ2012-2015 የኦዲት ግኝቶችን ገምግሟል። በኦዲት ግኝቱ ላይ የየተቋማቱ/መ/ቤቶቹ ኃላፊዎችና የግዥና ፋይናንስ ዳይሬክተሮቻቸው በኦዲት ግኝቱ ዙርያ ከክልል […]