17 ሚሊየን ሊትር ወተት፤8 ሚሊየን 815 ሺ እንቁላል፤636 ቶን የስጋ ምርት 26.17 ቶን የማር ምርት ተመርቷል፣
አንድ ሺ 130 ኩንታል የቡና ሰብል ማምረት ተችሏል፣
በሌማት ትሩፋት 3 የወተት፤4 የእንቁላል፤3 የአሳና 2 የማር መንደሮችን መፍጠር ተችሏል፣
በበጋ መስኖ የአትክልትና የሥራሥር ምርት በሁለት ዙር 2 ሺ 953 ሄክታር ማልማት ተችሏል፣
30ሺ 612 ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት ማቅረብ ተችሏል።
ለበጋ መስኖ ልማት 650 ኩንታል ምርጥ ዘር፣ 33 የውኃ መሳቢያ ሞተሮች ተሰራጭቷል፣
አንድ ሺ 800 አርሶ አደሮችንም የሰብል መውቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፣
በግሉ ዘርፍ 39ሺ 450 የዶሮ ጫጩቶችን ለማሰራጨት ተችሏል።
የአሳ ጫጩት ስርጭትን በተመለከተም 16 ሺ150 ጫጬቶችን ማሰራጨት ተችሏል፣
በክልሉ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማረጋገጥ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል
በክልሉ መንግስት በጀት ከ38 ሺ በላይ ተማሪዎችን ያቀፈ የትምህርት ቤት ምገባ ተግባራዊ ተደርጓል፣
በመርሐግብሩ ከ600 በላይ ለሚሆኑ የተማሪ ወላጆች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፣
ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ትኩረት በመስጠት 3ሺ 989 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፣
በ78 ማስተባበሪያ ጣቢያዎች ከ 2ሺ 600 በላይ ጎልማሶች የቀለም ትምህርት እንዲከታተሉ ተደርጓል፣
የመማሪያ መፅሀፍ ስርጭት ምጣኔን በዋና ዋና ትምህርቶች 1 መፅሀፍ ለአንድ ተማሪ ማድረስ ተችሏል፣
የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ተችሏል፣
አዳዲስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶቸ ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል፣
ከአንድ ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ዳር መብራቶች ተጠግነው ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል።
ባለፉት 6 ወራት በመንገድ ዳር ግብይት የሚፈጽሙ 2 ሺህ 261 ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ ተወስዷል
በከተማው በህገወጥ መንገድ ተወሮ የነበረ 2 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ወደ መንግስት እንዲመለስ ተደርጓል፣
የካቲት 19 ቀን 2017 ዓም