የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፈቲያ አብዱራህማን፣ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አብራሂም ሐሰን፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ከሪማ አሊ፣ በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ የተካሄዱ እና እየተካሄዱ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የኑር ፕላዛ መናፈሻን እንዲሁም በቅርቡ የተጀመረው የአባድር ፕላዛ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክትን ተመልክተዋል።
በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ እየተካሄዱ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች የአካባቢው ታሪካዊ ቅርስን ማዕከል ያደረገና ከነባር ዕሴት ጋር በተጣጣመ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ መመልከታቸውን የድሬደዋ ከተማና ሶማሊ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤዎች ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማቱ ለሌሎች አካባቢዎችም ምሳሌ መሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።




