የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ እያካሄደ የሚገኘው የተቋማት የ2017 የካፒታል ፕሮጀክት አፈፃፀም የመስክ ጉብኝት በዛሬው እለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ በዛሬው ዕለት የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኝቷል። የክልል ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ልዑክ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እያከናወናቸው የሚገኙ የካፒታል ፕሮጀክቶችን የተመለከቱ ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ጽ/ቤት እድሳትን፣ የረዥም ጊዜ መዝገቦችን ዲጂታይዜሽን የማድረግ ስራዎች እና የፍርድ ቤቶችን ችሎት ስማርት ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝቷል። የጠቅላይ ፍርድ […]