የክልል ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በክልሉ ማረምያ ኮምሽን ድንገተኛ ጉብኝት አካሄዱ።

በሐረሪ ክልል ምክር ቤት የህግ አስተዳደር እና ሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ኢማን መሀመድ የሚመራ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ በክልሉ ማረምያ ኮምሽን በመገኘት ድንገተኛ ምልከታ በማድረግ የኮምሽኑን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ዛሬ ጠዋት በክልሉ ማረምያ ኮምሽን ባካሄደው ድንገተኛ ጉብኝት በኮምሽኑ እየተከናወኑ የሚገኙ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ስራዎችን ጨምሮ የታራሚዎች አያያዝና መዝገብ አደረጃጀት፣ የስራ ክንውን ደረጃና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ተመልክተዋል።

በክልል ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሱት የተለያዩ ጥያቄዎች በማረምያ ኮምሽኑ የሰራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቷቸዋል።

በመጨረሻም በክልል ምክር ቤቱ የህግ አስተዳደር እና ሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ኢማን መሀመድ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን

በማረምያ ኮምሽኑ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችና የአገልግሎት ደረጃ ማሻሻያ ስራዎች አዘምኖ በማጠናከር በቀጣይ በአገልግሎት አሰጣት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ጨምሮ በቋሚ ኮሚቴው የተቀመጡ የማሻሻያ የስራ አቅጣጫዎችን በመውሰድ በትኩረት ሊሰራባቸውና የሚታዩ ክፍተቶችን በማረምና የመረጃና አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃዎችን አዘምኖ የማሻሻል ስራዎች በይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል የሚገባ መሆኑን አሳስበዋል።

**********

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት

የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/

➥ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hararicouncil/

➥ ቴሌግራም:▸ https://t.me/hararicouncil_info

➥ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/

➥ ትዊተር፦ https://twitter.com/hararicouncil

➥ ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/harari people regional council/

➥ ድረገጽ፦http://www.hararicouncil.gov.et/

Scroll to Top