የክልል ምክር ቤቱ የበጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ የ2012-2015 የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝቶችን እየተመለከተ ሲሆን በዚሁ መሰረትም በዛሬው ዕለት ቋሚ ኮሚቴው የክልሉን ፕላን ኮሚሽን፣ የህብረት ስራ ኤጀንሲ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ፣ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንን የ2012-2015 የኦዲት ግኝቶችን ገምግሟል።
በኦዲት ግኝቱ ላይ የየተቋማቱ/መ/ቤቶቹ ኃላፊዎችና የግዥና ፋይናንስ ዳይሬክተሮቻቸው በኦዲት ግኝቱ ዙርያ ከክልል ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የሐረሪ ክልል ምክር ቤት በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ፋቲሃ ሳኒ ግኝት የተገኘባቸው ተቋማትና ሴክተር መስሪያ ቤቶቹ በ15 ቀናት ውስጥ በግኘቶቻቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ግኝቶቻቸውን አስተካክለው ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
************
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት
የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/
➥ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hararicouncil/
➥ ቴሌግራም:▸ https://t.me/hararicouncil_info
➥ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
➥ ትዊተር፦ https://twitter.com/hararicouncil
➥ ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/harari people regional council/
➥ ድረገጽ፦http://www.hararicouncil.gov.et/
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን.
All reactions: