የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ከሐረሪ ክልል ምክር ቤት የጋራ ልምድ ልውውጥ አደረገ።

የልምድ ልውውጡ የምክር ቤቶቹን ግንኙነት በማጠናከር ህዝብን በፍታሀዊነት ለማገልገል ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል ።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና የስራ አመራሮች ከሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና የስራ አመራሮች ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የሐረሪ ክልል ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት የወከለንን ህዝብ በፍትሀዊነት በማገልገል የህዝብን ዕርካታ ለማረጋገጥ የክልል ምክርቤቶች በተለያዩ ጊዜያቶች የሚያደርጓቸው የልምድ ልውውጦች ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል ።

የሐረሪ ክልል ምክርቤት ም/አፈጉባኤ አቶ ሀሪፊ መሀመድ በበኩላቸው ስለ ሀረሪ ክልል ምክር ቤት አመሰራርት እና የአሰራር ስርአት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምክርቤቶች በህገመንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን በአግባቡ በመጠቀም ህዝብን በታማኝነት ለማገልገል በጋራ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

ልምድ ልውውጡ ለሁለቱም ክልል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልፀው በተለይም አጎራባች የክልል ምክርቤቶች የጋራ መድረክ በማዘጋጀት ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የሶማሌ ክልል ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን የሀረሪ ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴዎችም ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሶማሌ ክልል ምክርቤት አመራሮች በሐረር ቆይታቸው በከተማዋ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጨምሮ የአለም ቅርስ የሆነውን የጀጎል ግንብንም ተዘዋውረው ጎብኝቷል።

የሶማሌ ክልል ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተደረገላቸው አቀባበል እና እንደ ክልል ምክርቤት ይዘውት ለመጡት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሁም ልምድ እንዳገኙ ገልፀዋል ።

በልምድ ልውውጡም የሐረሪ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙሄዲን አህመድን ጨምሮ የሁለቱ ምክር በቶች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

************

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት

የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/

➥ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hararicouncil/

➥ ቴሌግራም:▸ https://t.me/hararicouncil_info

➥ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/

➥ ትዊተር፦ https://twitter.com/hararicouncil

➥ ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/harari people regional council/

➥ ድረገጽ፦http://www.hararicouncil.gov.et/

Scroll to Top