የክልል ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በማካሄድ ላይ በሚገኘው የፕሮጀክት አፈፃፀም ምልከታም በክልሉ ትምህርት ቢሮ እየተከናወኑ ያሉትን ፕሮጀክቶች ጎብኝቷል።
የልኡካን ቡድኑ በክልሉ ትምህርት ቢሮ እየተሰሩ በሚገኙት ፕሮጀክቶች ማለትም የአቡካር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ጂ+3) ማስፋፊያና የህጻናት ደህንነት፣ የአብነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማስፋፊያ ግንባታ፣ የመዋለ ህጻናት ት/ቤቶችን ፤ሀሰንጌይ ትምህርት ቤት እንዲሁም የክልሉ ትምህርት ቢሮ እድሳት. ጎብኝተዋል።
ሀሰንጌይ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት አፈፃፀም የፋይናንስ አፈፃፀም 60% የግንባታው ፊዚካል አፈፃፀም ደግሞ 86% መድረሱን፤ የአቡካር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት (ጂ+3) የግንባታው ፊዚካል አፈፃፀም ደግሞ 65% የፋይናንሺያል አፈፃፀም 50% መድረሱን፣ የአቡካር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ግንባታ (KG) ማስፋፊያ ስራዎች መጠናቀቁን;
የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማስፋፊያ (KG) ሞዴል ግንባታ የግንባታው ፊዚካል አፈፃፀም 100% እና 82% የፋይናንስ አፈፃፀም መድረሱን የክልሉ ትቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘካሪያ አብዱላዚዝ ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተው ገልፀዋል።
በመጨረሻም በክልል ምክር ቤቱ የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
13/5/2017
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት
የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/
➥ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hararicouncil/
➥ ቴሌግራም:▸ https://t.me/hararicouncil_info
➥ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
➥ ትዊተር፦ https://twitter.com/hararicouncil
➥ ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/harari people regional council/
➥ ድረገጽ፦http://www.hararicouncil.gov.et/
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን.





All reactions: