የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ በክልሉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እየተከናወኑ ያሉትን ፕሮጀክቶችን ስራ ሂደትና አፈፃፀም ሂደት ተመልክተዋል።
የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በክልሉ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እየተከናወኑ ያሉትን የካፒታል ፕሮጀክቶችን ማለትም የፈሳሽ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ፋብሪካ (ማከሚያ ጣቢያ) እና የንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ዝርጋታ ፕሮጀክት ስራዎችን ጎብኝቷል።
የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን እንደገለፁት በሶፊ ወረዳ በሃራዌ ቀበሌ ውስጥ ኢየተገነባ የሚገኘው የፈሳሽ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ ፋብሪካ (ማከሚያ ጣቢያ) ፕሮጀክት በ10 ሄክታር መሬት ላይ በ321 ሚሊየን ብር በጀት እየተገነባ የሚገኝ መሆኑንና ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ውስጥ ተጠናቆ በክልላችን ያለውን የፈሳሽ ቆሻሻ ችግር ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።
የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ፕሮጀክቱ የሚገኝበት ደረጃ አበረታች እና ተስፋ ሰጪ መሆኑን በመግለዕ ይህም የህብረተሰቡን የረዥም ጊዜ ጥያቄዎች የሚመልስ ነው ብሏል።
የክልሉ ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፋቲያ ሳኒ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዝ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎቱን መስጠት እስኪጀምር ድረስ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ መቀጠል የሚገባ መሆኑን አሳስበዋል።
በተመሳሳይ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በክልሉ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እየተከናወነ ያለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ዝርጋታ ፕሮጀክትን የጎበኙ ሲሆን የክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ እየተከናወኑ ከሚገኙ ስራዎች በተጓዳኝ የማስፋፍያ ስራዎች ላይ በይበልጥ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስቧል።
በመጨረሻም የክልሉ ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፋቲያ ሳኒ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
**********
14/5/2017
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት
የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/
➥ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hararicouncil/
➥ ቴሌግራም:▸ https://t.me/hararicouncil_info
➥ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
➥ ትዊተር፦ https://twitter.com/hararicouncil
➥ ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/harari people regional council/
➥ ድረገጽ፦http://www.hararicouncil.gov.et/
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን.




All reactions: