የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ በዛሬው ዕለት የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኝቷል።
የክልል ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ልዑክ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እያከናወናቸው የሚገኙ የካፒታል ፕሮጀክቶችን የተመለከቱ ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ጽ/ቤት እድሳትን፣ የረዥም ጊዜ መዝገቦችን ዲጂታይዜሽን የማድረግ ስራዎች እና የፍርድ ቤቶችን ችሎት ስማርት ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝቷል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ጽሕፈት ቤት እድሳት 16.9 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ሲሆን የፊዚካል አፈጻጸም ደረጃው 93 በመቶ መድረሱን እና ለረጅም አመታት ሲሰሩ የነበሩ የፍርድ ቤት መዝገቦችን ወደ ዲጂታይዝ ለማድረግ እና የፍርድ ቤቶችን ችሎት ለማዘመን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ የጵ/ቤቱ ሃላፊና የማኔጅመንት አባላት ገለፁዋል።
በመጨረሻም በሐረሪ ክልል ምክር ቤት የሴቶችና ህጻናት ህግ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ኢማን መሀመድ የፍርድ ቤቶችን ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች ነው ብለዋል።
በተለይም የጠቅላይ ፍርድ ቤት እድሳት በጥራትና በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቅ እንዳለበት፣የፍርድ ቤት መዝገቦችን ማዘመን የመዝገቦችን መጥፋት ለመከላከል ትልቅ ሚና የሚጫወት በመሆኑ መዝገቦችን ዲጂታይዜሽን የማድረግ ስራ እንዲሁም የፍርድ ቤቱን ክፍል (ስማርት ችሎት ክፍል) የማዘመን ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
**********
15/5/2017
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት
የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/
➥ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hararicouncil/
➥ ቴሌግራም:▸ https://t.me/hararicouncil_info
➥ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/
➥ ትዊተር፦ https://twitter.com/hararicouncil
➥ ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/harari people regional council/
➥ ድረገጽ፦http://www.hararicouncil.gov.et/
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን.




All reactions: