የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ጎበኘ።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ጎበኘ።

*******

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ልዑክ በሐረር ከተማ እየተዘረጋ ያለውን የሲሲቲቪ ካሜራ የቁጥጥር ሥርዓትና የተገዙ ዕቃዎችን ጎብኝቷል።

የሲሲቲቪ ካሜራ ፕሮጄክት በህዳር 2016 በጠቅላላ 115 ሚሊዮን ብር በጀት የተጀመረ ሲሆን የፕሮጀክቱ ፊዚካል አፈፃፀም 80 በመቶ መድረሱን ለቋሚ ኮሚቴው ገለፃና ማብራርያ የተደረገ ሲሆን የሐረር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሲሲቲቪ ካሜራዎቹን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ተግባራዊ እየተደረገ ስለመሆኑና ፕሮጀክቱም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተገልጷል።

በሀረሪ ክልል ምክር ቤት የሴቶችና ህጻናት ህግ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ኢማን መሀመድ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን በዚህም፤

• የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቱ ጥራትና ደረጃውን ጠብቆ በፍጥነት ማጠናቀቅ እንዲቻል በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ በጋራ መርሃ ግብር ላይ ትኩረት አድርገው መስራት የሚገባ መሆኑን።

• ሀረር ከተማን “ስማርት” የማድረግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ቀደም ሲል በወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ያደረገውን ጉብኝት መነሻ በማድረግ የማጠቃለያ ውይይት አካሂዷል።

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላትና ሰብሳቢዎች በክልሉ ውስጥ ያሉት የወረዳው ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዝርዝር ያነሱ ሲሆን ችግሮቹን ለመፍታት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የማኔጅመንት አባላት ገልፀዋል።

በመጨረሻም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሴቶችና ህጻናት ህግ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ኢማን መሀመድ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

**********

15/5/2017

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት

የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት/

➥ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hararicouncil/

➥ ቴሌግራም:▸ https://t.me/hararicouncil_info

➥ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/

➥ ትዊተር፦ https://twitter.com/hararicouncil

➥ ፍለከሪ፡-https://www.flickr.com/photos/harari people regional council/

All reactions:

Scroll to Top