ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የ ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንደገለፁት የመስኖ መሰረተ ልማት፤የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮችን በማስፋት፤የማካኔዜሽን አጠቃቀምና የምርጥ ዘር አቅርቦትን በማሳደግ የግብርና ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰቶ ተሰርቷል።

በዚህም በብርዕና አገዳ ሰብሎች 9 ሺ 159 ኩንታል በማልማት 246 ሺ 800 ኩንታል ምርት ማምረት መቻሉን ገልፀዋል።

ምርቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 34 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ገልፀዋል።

የጥራጥሬ ሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራም 3 ሺ 390 ኩንታል ቦሎቄ፤46 ሺ 272 ኩንታል የሎዝ እና 199 ሺ 202 ኩንታል የፍራፍሬ ምርት መሰብሰብ ተችሏል።

እንዲሁም የአንቂ ሰብሎችን ምርታማነት ለማሳደግ በተሰራው ስራ 1 ሺ 130 ኩንታል የቡና ሰብል ማምረት ተችሏል።

በሌማት ትሩፋት ፕሮግራም በተሰሩ ስራዎችም 3 የወተት፤4 የእንቁላል፤3 የአሳ እና 2 የማር መንደሮችን መፍጠር መቻሉን በሪፖርቱ አቅርበዋል።

በዚህም 17.1 ሚሊየን ሊትር ወተት፤8 ሚሊየን 815 ሺ እንቁላል፤636 ቶን የስጋ ምርት 26.17 ቶን የማር ምርት ማምረት መቻሉን አክለዋል

በበጋ መስኖ የአትክልትና የሥራሥር ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተሰራው ስራም

በሁለት ዙር 2 ሺ 953 ሄክታር ማልማት ተችሏል።

የሰብል ግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀምን ለማሻሻልም 8 መቶ ኩንታል ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ፤30ሺ 612 ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት ማቅረብ ተችሏል።

ለበጋ መስኖ ልማት በተሰጠው ትኩረትም 650 ኩንታል ምርጥ ዘር እና የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን ሊያጎለብቱ የሚችሉ 33 የውሃ መሳቢያ ሞተሮች፣ 30 ዲናሞዎች፣ 30 የውሃ ማቆሪያ ሸራ እና 3 የውሃ ፓምፖች ተሰራጭተዋል።

1 ሺ 800 አርሶ አደሮችንም የሰብል መውቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

የእንስሳት ግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀምን ለማሻሻል በተሰራው ስራም 3ሺ 743 ላሞችን በሰው ሰራሽ ዘዴ በማዳቀል 1ሺ 563

ጊደሮች እንዲወለዱ ተደርጓል በለዋል።

በክልሉ የዶሮ ብዜትና ስርጭት ማዕከል 6 ሺ 697 ዶዎችን ማቅረብ መቻሉን እንዲሁም በግሉ ዘርፍ 39ሺ 450 የዶሮ ጫጩቶችን ለማሰራጨት ተችሏል።

የአሳ ጫጩት ስርጭትን በተመለከተም 16 ሺ150 ጫጬቶችን ማሰራጨት መቻሉን ጠቁመዋል።

የገጠር ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራም በቋሚ ቀጥተኛ ድጋፍ 6 ሚሊየን 666 ሺ 400 ብር እንዲሁም በቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ለታቀፉ ተጠቃሚዎች 2 ሚሊየን 396 ብር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የህብረት ሥራ ማህበራትን በተመለከተም 2 ሺ 2 85 አባላትን ያቀፉ 23 ማህበራት መደራጀታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርቱ አመላክተዋል።

+4

All reactions:

Scroll to Top