-የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ።
ምክር ቤቱ የክልሉን መስተዳድር ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም የግማሽ አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበት እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
በሚቀርቡ የተለያዩ አጀንዳዎች፤አዋጆችና እና ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ላይ በመምከር ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።
በጉባዔው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት አባላት እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተግኝተዋል።



All reactions: