የሐረሪ ክልል ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል።
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔው ላይ መደበኛ እና ካፒታል ወጪዎችን ለመሸፈን በቀረበው 665 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ላይ በመወያየት አፅድቋል።
ምክር ቤቱ ካፀደቀው በጀት 427 ነጥብ 4 ሚሊየን ብሩ ለመደበኛ እንዲሁም 238 ሚሊየን ብሩ ለካፒታል ፕሮጀክቶች እንደሚውልም ተመላክቷል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ከአዲስ ተሻሎ በቀረበው የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ እና የክልሉ ፍርድ ቤት ሰራተኞች ረቂቅ ደንብ ላይ በመወያየት የቀረቡ ደንቦችን በማፅደቅ የምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔው አጠናቋል።





All reactions: