ሰው ተኮር ተግባራትን በማጠናከር የአቅመ ደካሞችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ገለፁ።

የክልሉ ምክር ቤት በኤረር ወረዳ ሀዋዬ ቀበሌ በ600 ሺ ብር ወጪ ያስገነባውን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት የማስረከብ ስነ ስርዓት አካሂዷል ፡፡

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት በኤረር ወረዳ ሀዋዬ ቀበሌ ከ600 ሺ ብር ወጪ ያስገነባውን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት የማስረከብ ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም የክልሉ መንግስት ለበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተለይም ብልፅግና ፖርቲ ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በዚህም ለአቅመ ደካማ ዜጎች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

አቅመ ደካሞችን መደገፍ የሁልጊዜ ተግባር ሊሆን ይገባል ያሉት አፈ ጉባኤው ለህዝቡ ወገንተኝነታችንን የምናሳይበት ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ በበኩላቸው ቤት መገንባት ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡን ኑሮ እንዲሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ለአቅመ ደካማ ዜጎች በትምህርት ዘርፍም የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎች ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

ቤት የተገነባላቸው አርሶ አደር አቶ አሊ ሙሳ የመኖሪያ ቄያቸው ቀደም ሲል ለኑሮ አስቸጋሪ የነበረ መሆኑን ገልፀው አሁን በአዲስ መልኩ ስለተገነባላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል ፡፡

በስነስርአቱ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ የካቢኔ አባላት እና ሌሎች አመራሮችና እንግዶች ተገኝተዋል።

Scroll to Top