የኢትዮጲያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ብሔር ብሔረሰቦች እሴቶቻአቸውን የሚያጋሩበት እንዲሁም ህብረ ብሄራዊ አንድነታቸውን የሚያፀኑበት መሆኑ ተገለፀ።
በየዓመቱ ህዳር 29 የሚከበረው የኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር ቆይቷል በዛሬው እለት የማጠቃለያው መርሀ-ግብር ተከናውኗል፡፡ በማጠቃለያው መድረክም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን፣ የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅ/ፅ ቤት […]