የድሬደዋ ከተማና ሶማሊ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤዎች በሀረር ከተማ የኑር ፕላዛ፣ የአባድር ፕላዛ ፕሮጀክት እና ሌሎች የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎበኙ።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በተገኙበት የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፈቲያ አብዱራህማን፣ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አብራሂም ሐሰን፣ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ከሪማ አሊ፣ በጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ የተካሄዱ እና እየተካሄዱ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።በጉብኝቱም የኑር ፕላዛ መናፈሻን እንዲሁም በቅርቡ የተጀመረው የአባድር […]