የክልል ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች እና አባላት የክልሉን የእርድ አገልግሎት መሰጫ ማዕከል (ቄራ) የስራ ሂደት ተመለከቱ።
********
በሐረሪ ክልል ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቶ ጅብሪል መሀመድ የተመራው የክልል ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች እና አባላት የክልሉን የእርድ አገልግሎት መሰጫ ማዕከል (ቄራ) እርድ በሚከናወንበት የስራ ሰዓት እኩለ ለሊት 6:00 ላይ በመገኘት የማዕከሉን ስራ ሂደት ተመልክተዋል።
በጉብኝቱም የቄራ አገልግሎት ማዕከሉ አጠቃላይ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችና የግንባታ ሂደቱን በተመለከተ ገለጻና ማብራርያ የሰጡት የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኤሊያስ ዮኒስ ሲሆኑ ዘመናዊ የእርድ አገልግሎት መሰጫ ማዕከሉ በዘርፉ የሚታዩትን በርካታ ችግሮች ለመቅረፍ በሚያስችለው መልኩ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገለፀዋል።
በተለይም ለክልሉ ነዋሪ የሚቀርቡ ንፁህ እና ጤናማ የስጋ አቅርቦት ጎን ለጎን ለማዕከሉ መሟላት ያለበትን ተጨማሪ ግብዓቶችና በማከል የሚሰጠውን አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ክልሉ በዘርፉ የሚያገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻ የምክር ቤቱ የኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በአቶ ጅብሪል መሀመድ ጨምሮ በአባላቱ የቄራ ማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ ሊያሳልጡ የሚችሉ አሰራሮችን በመጠቀም እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት የሚታዩ ውስንነት እና ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
************
ታህሳስ 2/2017 ዓ/ም




