በክልሉ 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ሀገራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ እየተከበረ ነው :-አቶ ሱልጣን አብዱሰላም

19 ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ሀገራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ገለፁ።

በሀረሪ ክልል 19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበርን በተመለከተ ከበዓሉ አብይ ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አንዱሰላም በውይይቱ ላይ እንደገለፁት የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ሀገራዊ መግባባትና አንድነትን ይበልጥ በሚያጎለብት መልኩ እየተከበረ ነው።

ዕለቱ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ያላቸውን ማንነት፣ ባህል፣ ወግ እና ታሪክ በአደባባይ በማውጣት በአንድነት እያከበሩ ይበልጥ የሚቀራረቡበት መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተከበሩት በዓላት የወል ትርክቶችን የበላይ እንዲይዙ በማድረግ የዕርስ በርስ ግንኙነትን በማጎልበት ና አገራዊ ገፅታን በመገንባት ረገድ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።

በቀጣይም ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ በማግልበት ዘላቂ ሰላምን በማስፈን የተገኙ የብልፅግና ግቦችን ለማስፋት ርብርቡ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ በበኩላቸው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል መከበሩ ሀገራዊ አንድነትን ለማጎልበትና የጋራ ትርክትን ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽዎ የሚያበረክት ነው ብለዋል።

በተለይ ለማህበረሰቡ የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮትን በማስገንዘብ አብሮነትና ወንድማማችነት ይበልጥ እንዲጎለብት እያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል።

የተፈጠረው የወንድማማችነት እና አብሮነት እሴት አገራዊ የብልፅግና ትልሞችን ለማሳካት እና ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር የተጀመሩ ስራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የሚያስችል እንደሆነም ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሃመድ፣ የሀረሪ ጉባኤ ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪምን ጨምሮ የምክር ቤቱ፤የክልል ሴክተር መስሪያ ቤት እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

19 / 03 / 2017

All reactions:

17Bahar Abdi, Juliyan Abdi and 15 others

Scroll to Top